.png)
አዲስ አበባን የህክምና ቱሪዝም ለማድረግ እየተሰራ ነው" አቶ አብረሃም ታደሰ
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የቂርቆስ ጤና ጣቢያ መርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አደረጉ።
እንደ አዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት ብቻ የህዝቡን የህክምና ፍላጎት ለማርካትና እስታንዳርዳቸውን ለማስጠበቅ ከተገነቡ 28 የህክምና ማዕከላት 22 ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ ብለዋል አቶ አብረሃም በምረቃው ወቅት
ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩ ለጤናው ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ነው ያሉት አቶ አብረሃም እነዚህ ፕሮጀክቶች ለመጭው ትውልድ የሚተላለፉና የህብረተሰቡን ጥያቄ የሚመልሱ በመሆናቸው ህብረተሰቡ እንደ ዓይኑ ብሌን ሊጠብቃቸው ይገባልም ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ቀዳሚ አጀንዳው አዲስ አበባን የህክምና ቱሪዝም ማድረግ ነው ያሉት ኃላፊው ዛሬ በከተማችን የተመረቁት 28 የህክምና ማዕከላት ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
እንደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማም ዛሬ መርቀን ለህዝብ አገልግሎት ያዋልነው የህክምና ማዕከል የከተማ አስተዳደሩ የፕሮጀክት አካል በመሆኑ ለዚህ ስኬት የተጉ አመራሮችና መላው ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ በበኩላቸው ከተማዋ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሰራችው ስራዎች እጅግ አስደማሚ መሆናቸውን ገልፀው ይህ ውጤት የተመዘገበው ለልማት የቆረጡ አመራሮችና ነዋሪ ስላለን ነው ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.