.png)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተገነቡ 28 የጤና ፕሮጄክቶች መካከል በዛሬው እለት 22 የጤና ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለጤናው ዘርፍ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ የጤና ተቋማት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ በባለፉት ጊዜያት የከተማዋን ነዋሪ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የወጣቶች ስፖርት ማዝወተሪያ ፣ የትምህርት ተቋማት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ያሉ ሲሆን በዛሬው ዕለት የጤና ተቋማት እያስመረቅን እንገኛለን ብለዋል።
ፕሮጀክቶቹ ለህዝብ ጥያቄ ቅድሚያ የሰጠንበት ነው
ቃል የገባነውን በተግባር ፣ በፍጥነት ተግብረን ህዝባችን ጋር የደረስንበት ለህዝብ የገባነውን ቃል መተግበራችንን የሚያሳዩ እንዲሁም ሁሌ በሰራነው ሳንረካ ይልቁኑ በተገኘው ውጤት እየበረታን የህዝብ አገልጋነታችንን በተግባር እያረጋገጥን ይበልጥ ለመስራት የምንተጋ ስለመሆኑ ህያው ምስክር ናቸው ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው በክፍለ ከተማችንም በተከናወኑ ስራዎችም የጤና ተቋማትን ለአገልግሎት ምቹ ፣ ማራኪና ሳቢ በሆነ አካባቢ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የእናቶችንና የህጻናት ሞት ለመቀነስ ፣ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም እውን ለማድረግ ፣ ህብረተሰቡ በሽታዎችን ቀድሞ የመከላከል የመቆጣጠር ስራዎች እንዲያሻሽሉ
በዛሬው ዕለት ለምርቃት ያበቃናቸው የጤና ተቋማት ግንባታዎች አስተዳደሩ ለጤናው ዘርፍ የሰጠውን ልዩ ትኩረት ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን ጤና ተቋማት ለታካሚዎች ምቹ ሁኔታ የፈጠሩ ፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍና የጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው።
ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠት በመሆኑ የጤና ባለሙያዎች ህይወት ሰጥታችሁ ህይወት የምታድኑ በመሆናችሁ በተፈጠረላችሁ ምቹ የስራ ከበባቢን በመጠቀም የህብረተሰባችንን የጤና አገልግሎት እንድንጠብቅ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በፕሮጀክቱ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላትና ተቋማት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል በተያያዘም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተክለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.