ጤናማ ዜጋ ለመገንባት የሚያስችሉ የጤና ተቋማት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጤናማ ዜጋ ለመገንባት የሚያስችሉ የጤና ተቋማት ግንባታና ማስፋፍያ የዘርፉ ትልቅ ገፀበረከት እንደሆነ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት በከተማ አስተዳደሩ ከተገነቡ 28 የጤና ፕሮጄክቶች መካከል በዛው እለት  22 አስመርቀናል ::በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለበርካታ ዘመናት የማህበረሰቡ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት ጥያቄ የነበረዉን የአቃቂ ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ የከተማ እና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የምርቃት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ የከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልፀው በዛሬው ዕለትም በከተማዋ 22 የጤና ፕሮጀክቶች በመገንባትና ሙሉ ዘመናዊ ቁሳቁሶችን በሟሟላት ለማህበረሰቡ ክፍት መደረጋቸውን ገልፀው እነዚህ ጤና ጣቢያዎች ዘመኑን የዋጁ የጤና መገልገያዎችን ያሟሉ የከተማዋን ስማርት ሲቲ ግንባታ ጉዞ የሚያረጋግጡ ለበርካታ ዘመናት የማህበረሰቡ የመልካም አስተዳደር እና የጤና አገልግሎት ጥያቄ መመለስ የተቻለበትና ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ ያገኘውን ይሁንታ በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑን በማንሳት ፕሮጀክቱ ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚሻ ጠቁመዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው ምርቃቱን ልዩ የሚያደርገው ክ/ከተማው ካሳካው ድል ማግስት መደረጉ መሆኑን በማንሳት ጤና ጣቢያው ከዚህ ቀደም በተጣበበ ሁኔታ ለበርካታ ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ የነበረ መሆኑን እና የጤና ጣቢያው ማስፋፊያ ፕሮጀክት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈታ ፣ ፍትሃዊ የጤና ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ ፣ ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋን ለማፍራት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው ጤና ጣቢያው ባለ 5 ወለል ህንፃና የራሱ የሆነ የስልጠና ማዕከል ያለው ፣ የጥርስ የቆዳ የቀዶ ጥገና ህክምናን የሚሰጥ ተጨማሪ በአዲስ መልክ የሚሰጥ ለአገልጋይና ለተገልጋይ ምቹ ሁኔታ የፈጠረና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረው የመጣውኝ ውጤት እንደ እርሾ በመጠቀም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት ስኬቶችን ማላቅ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በመጨረሻም ከምርቃት ስነ-ስርዓቱ ጎን ለጎን ኃላፊዎቹ በጤና ጣቢያው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.