ከተማችንን የምንሰራት ፣ ጤናማ ትውልድ እንዲገነ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከተማችንን የምንሰራት ፣ ጤናማ ትውልድ እንዲገነባ፣ እንዲረከባት እና እንዲያበለፅጋት ነው !

በ2017 በጀት ዓመት ከገነባናቸዉ 28 የጤና ፕሮጀክቶች  መካከል 22 ያህሉን በዛሬው እለት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

በሁሉም ክፍለ ከተሞች ዛሬ አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግናቸው የጤና ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት  ጋር እኩል ደረጃ ያላቸው ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት ከፍ እንዲል ከ4 ቢልዮን በላይ ወጪ የተደረገባቸዉ በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ግብአት እና ባለሙያዎች ጭምር  እንዲደራጁ ተደርገዋል ።

እነዚህም ለከተማችን ነዋሪዎች ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ፤ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም በቅንነት፣ በትጋት እና በታማኝነት የማገልገል ማሳያችን ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲበቁ ያደረጋችሁ በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.