.png)
የንግድ ተቋማት የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ የከተማዋን ፈጣን ዕድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴን ይበልጥ እንደሚያሳድግ ተጠቆመ።
የአዲስ አበባ ከተማ የህገወጥ ንግድ ቁጥጥርና የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የንግድ ተቋማት የምሽት ግብይት የወጣውን ደንብ ተግባራዊ መደረጉን ምልከታ አካሒዷል።
በአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና በንግድ ቢሮ ሀላፊ በወ /ሮ ሀቢባ ሲራጅ የተመራ የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የንግድ ተቋማት የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በምልከታውም የከተማውና የክፍለ ከተማው የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል አባላትም ተገኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ዓላማ የንግድ ተቋማት በመንግስት በተቀመጠላቸው የሥራ ሰዓት ገደብ ክፍት ሆነው በአገልግሎት ላይ መሆናቸውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ነው።
የወጣውን ደንብ ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሆነም ተጠቅሷል።
በጉብኝቱም የተቋማት የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ የከተማዋን ፈጣን ዕድገት ተከትሎ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴን ይበልጥ እንደሚያሳድግ ተብራርቷል።
የምሽት ንግድ አገልግሎት መስፋፋት የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ በማነቃቃት የዜጎችን ገቢ ከፍ ከማድረግ ባለፈ ለተጨማሪ የሥራ ዕድሎች መፈጠርና የስራ ባህልን እንደሚያሳድግም ተመላክቷል።
በምልከታው በአዲስ አበባ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ፤በንግድ ቢሮ ሀላፊ በወ /ሮ ሀቢባ ሲራጅ ፤የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዲሁም የኮልፌ ክ/ከተማ ወ/ሮ ኒእመተላህ ከበደ ተገኝተዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.