አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በበጀት አመቱ ባስመዘገበው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በበጀት አመቱ ባስመዘገበው ስኬት ልዩ ተሸላሚ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ተቋማት እውቅና የሰጠ ሲሆን፣ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም በበጀት አመቱ ባስመዘገበው ስኬት ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት አመት የህዝብ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎች እንዲመለሱ እንዲሁም ነዋሪውን ህብረተሰብ ከአስተዳደሩ ጋር በማገናኘት ረገድ ውጤታማ ስራ ማከናወኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

ከንቲባዋ አክለውም፣ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲመለሱ እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች እንዲመለሱ ህዝብ በቀጥታ ከአመራሩ ጋር የሚወያይባቸው ዋርካ እና አገልጋዩን የመሳሰሉ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ የከተማውን ነዋሪ እና አስተዳደሩን በማገናኘት ረገድ ስኬታማ ተግባር ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ሚዲያው፣ ተወዳዳሪነቱን በማሳደግ በከተማው የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን እስከ ታች ወርዶ በመስራትና ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ረገድም ውጤታማ መሆኑንም ነው ከንቲባ አዳነች ያመላከቱት።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በበኩላቸው፣ ሚዲያው በተለያዩ አማራጮች መረጃዎችን ለህዝብ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሀይል ራሱን በማብቃት እንዲሁም ብዝሃነትን በጠበቀ መልኩ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

የተገኘው ውጤት አመራሩ እና ሰራተኛው ተናበው በጋራ ባደረጉት ርብርብ መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠን እውቅና አደራም ጭምር በመሆኑ ለቀጣይ በጀት አመት ጥንካሬያችንን በማስቀጠል የተሻሉ ስኬቶችን ለማስመዝገብ ተነሳሽነትን የጨመረልን ነው ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.