
"የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠው ትኩረት የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋ በፅኑ መሰረት ላይ የሚጥል ነው።" ኢ/ር ወንድሙ ሴታ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመልሱ በርካታ ፕሮጀክቶችን መገንባት መቻሉንና የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት በበጀት ዓመቱ ከ5.2 ቢሊየን ብር በላይ በመመደብ በርካታ ትምህርት ቤቶችና የአይሲቲና ሌሎች የትምህርት መሰረተ ልማት መገንባት መቻሉንና በዚህም የተማሪ ጥምርታን በመቀነስ ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን አንስተው የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠው ትኩረት የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋ በፅኑ መሰረት ላይ የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በክፍለ ከተማው ልማትን ባህል በማድረግ በርካታ ትልልቅ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በማህበረሰቡና በባለሀብቱ ተሳትፎ እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቅሰው አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ጥራት ፣ ፍትሀዊ ተደራሽነትና ለማረጋገጥ በ2017 በጀት ዓመቱ የብልፅግና ማሳያ የሆኑ 21 የትምህርት ፕሮጀክቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ ማስመረቅ መቻሉንና አንስተው ህብረተሰብም ሆነ ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቶቹ ጉዳት እንዳይደርስባቸውና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ ሊንከባከባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም ከምርቃት መርሃ-ግብሩ ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ የመትከል ፕሮግራም ተከናውኗል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.