.png)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ 150 ፕሮጀክቶችን አስመረቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የትምህርት ቤቶችን የመሰረተ ልማት ለማሻሻል ባወጣው እቅድ መሰረት ከፍተኛ በጀት ተመድቦባቸው የተገነቡ 150 ፕሮጀክቶች ባዘሬው እለት ተመርቀዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ ተገኝተው ፕሮጀክቶቹን በይፋ ሲያስመርቁ እንደተናገሩት የተገነቡት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።
አቶ ጥራቱ አክለውም እነዚህ ፕሮጀክቶች የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ባሻገር ለትውልድ ግንባታ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አስታውቀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፍ ላይ ትኩረት በማድረግ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑንም ተናግረዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በበኩላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡአስተዋፅኦ ላደረጉ የተለያዩ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በዛሬው እለት የተመረቁ ፕሮጀክቶችም በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ተማሪዎች የተሻለ የመማሪያ አካባቢ በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋ፡፡
በቀጣምይ በክፍለ ከተማው የትምህርት ተደራሽነትን የማስፋት እና የመሰረተ ልማት የማሻሻል እንደሚሰራ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አብራርተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.