.png)
ከሁሉም በላይ የረዳን ፈጣሪ የተመሰገን ይሁን !
በ2017 በጀት አመት በ5 .2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸዉን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች መርቀን ለአገልግልሎት ክፍት አድርገናል ።
ፕሮጀክቶቹ በጥራትና ደረጃቸዉን ጠብቀዉ የተሰሩ 14 አዳዲስ ትምህርትቤቶች ፤ በ64 ነባር ትምህርትቤቶች ላይ ማስፋፋያ የተገነቡ 1655 የመማሪያ ክፍሎች ፣ የአይሲቲ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፅሀፍቶች ፣ የስፖርት ሜዳዎች ፣ ምድረጊቢዎችን ፅዱ ፣ ዉብ የማድረግ ፣የመጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ አገልግሎት ጨምሮ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና መምህራን ምቹ የማድረግ ስራዎችን ያካተተ ነዉ፡፡
ትውልድን ለማነጽ በተሰራው ስራ አብራችሁን የሰራችሁትን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩኝ እነዚህ ትምህርትቤቶች የእናንተ እና የልጆቻችሁ ሀብት በመሆናቸው እንድትንከባከቧቸው አደራ እላለሁ፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.