
ህይወት አድን ስራ በፈጣሪም በሰዉም ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለዉ።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ170 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለኩላሊት ህሙማን 20 የዲያሊሲስ ማሽን እና 10 ዘመናዊ አልጋዎችን በማቅረብ ለ180 ታካሚዎች ለ3 አመት የሚሆን የዳያሊስስ ግብዓቶች ከወንበሮች ጋር አስረክቦናል።
ከፍለዉ መገልገል ለማይችሉ 144 ታማሚዎች በምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ እና ዘዉዲቱ ሆስፒታሎች በየአመቱ እስከ 25 ሚሊየን ብር በመመደብ የዛሬ አምስት ዓመት ያስጀመርነዉ ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ላይ የዛሬዉ ድጋፍ ሲጨመርበት አገልግሎቱን በእጥፍ ለማሳደግ ስለሚያስችለን ለታካሚዎቻችን ትልቅ እፎይታ ነው።
የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በህሙማን፣ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም እጅግ አድርጌ እናመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.