
የኢትዮጵያ ብልፅግና ከዳር እስከ ዳር እስኪዳረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራታችንን እንቀጥላለን !
በዛሬው የአሶሳ ጉበኝታችን አዲሰ አበባ ላይ ከዓመት ዓመት ባህል እየሆነ የመጣውን የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ፣ የምገባ ማዕከል ማቋቋም ፣ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አካል የሆነው የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች ግንባታን እና የፅዱ ኢትዮጵያ ሥራዎችን አሶሳ ከተማ ላይ አስጀምረናል ።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የስራ አቅጣጫ መሰረት የአዲስ አበባን አሮጌ ገጽታ እና የድህነት ታሪክ ለመቀየር በመልሶ ማልማት እና በኮሪደር ልማት ስራ ከህዝብ ውይይት እስከ ትግበራ 24/7 በመስራት እንዲሁም ህዝባችንን የልማቱ ባለቤት በማድረግ ያመጣነውን ተጨባጭ ወጤት እና ተሞክሮዎቻችንን አካፍለናል።
ወደ ክልሎች እየተስፋፋ ያለውን እና በአሶሳ ከተማ እየተሰራ ያለዉን የኮሪደር ልማት የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አሻድሊ ሃሰን አስጎብኝተውናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.