.png)
ማምሻዉን የምዕራቧ ኮከብ በሆነችው በቤኒሻንጉል አሶሳ ከተማ ከወንድሜ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራችንን አኑረናል ::
በአሶሳ ከተማ "ሀለዋ የአግሮ ኢንዱስትሪ" መንደር በ60 ሄክታር ላይ ያረፈውን የሌማት ቱሩፍት የሆነውን የዶሮ ፣ የእንቁላል እና የወተት ተዋፅኦ በቀላል መንገድ በማልማትና የአካባቢ ሀብትን በመጠቅሞ እንዴት ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል ተዘዋውረን ጎብኝተናል::
አዲስ አባባ ከክልሎች ጋር የምርት አቅርቦት ትስስር በመፍጠር ምርትን ወደ ከተማዋ እንዲገባ እየሰራች ትገኛለች በቀጣይም በኮሪደር ልማት የተሰሩትን ስራዎች ልምድ ልዉዉጥም የምናደርግ ይሆናል።
ስለ ተደረገልን ደማቅ አቀባበል እናአመሰግናለን !
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.