
የተጀመሩ ተስፋ ሰጪና አበረታች ውጤቶችን በማስቀጠል የ2018 በጀት ዓመት እቅድ የትኩረት አቅጣጫዎች፤ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች
👉የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም አጠናክሮ የማስቀጠል፣
👉በፕሮጀክቶች አፈፃጸም ያገኘነዉን ድል በአገልግሎትና መልካም አስተዳደር መድገም፤
👉የአዲስ መሶበ Vertual Service አንድ ማዕከል አገልግሎትን ማስፋትና ማጠናከር፤
👉የገቢ አሰባሰባችንን በማዘመን የገቢ እቅድ ማሳካት፤
👉 የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በግል ዘርፉ፣በሕብረት ሥራ ማኅበራት፣በመንግስትና በግል የአጋርነት ፕሮግራም በስፋት ተግባራዊ ይደረጋል፤
👉የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ የሌማት ትሩፋትና የከተማ ግብርናን ስችንን ማስፋት፤
👉 የውሃ አቅርቦትና የተጀመሩ ሜጋ ኘሮጀክቶችን በመሟላ ሁኔታ ለማጠናቀቅ መስራት፤
👉የተጀመረዉን የትምህርት ሪፎርም በማጠናከር የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ
👉የጤና አገልግሎት ይበልጥ የማሻሻልና የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣
👉 የወጣቶች የሥራ አድል እና አምራች ኢንዱስትሪን የማስፋትና ተወዳዳሪነቱን የማሳደግ ስራ በልዩ ትኩረት ይከናወናል፤
👉 የሕብረተሰብ ተሣትፎና የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን አጠናክሮ ማስቀጠል፡
👉 በከተማችን ጽዳትና ውበት መስክ የተገኘዉን ስኬት በማላቅ ከምንጊዜውም በላቀ ትኩረት ይሰራል፤
👉የከተማችንን የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ይበልጥ በማስተዋወቅ እና እንዲጎበኙ በማድረግ ከዘርፉ ከተማችን ማግኘት የሚገባትን ሁለንተናዊ ፋይዳ እንድታገኝ ማድረግ፤
👉ሌሎች የሰው ተኮር ስራችንን ህዝባችንን እያሳተፍን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
👉ለአገራችን ዘላቂ ሠላም እና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ ላይ በትጋት ይሰራል፤
👉ነጻ፣ ሠላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
👉 በአጠቃላይ ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፍ ሚናዋን በብቃት የምትወጣ ስሟና ግብሯ የተናበበ ስማርት ከተማ እንድትሆን የጀመርነዉን ልማት በጥራት፣ በስፋትና በፍጥነት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2018 እቅድ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቀቀ::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.