3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዓመት የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የከተማ አስተዳደሩ የ2018 በጀት ዓመት በጀት 350 ቢሊየን ብር ለምክር ቤት ቀርቦ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በሁለተኛው ቀን ወሎ  በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ -አብዱልቃድር ሬድዋን ለ2018 በጀት ዓመት 350 ቢሊዮን ብር በእቅድ መያዙን  አቅርበዋል::
 
ከተመደበው በጀት ውስጥ ለካፒታል በጀት 249.9 ቢሊዮን ብር እና ለመደበኛ ወጪ 100.1 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ 350 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምጽ  አፅድቋል፡፡ 

ባቀረቡት የበጅት ድልድል የ2018 በጀቱ በዋናነት ለደህነት ቅነሳ፣ ለዘላቂ ልማት፣ የስራ እድል ፈጠራ   ትላልቅ ፕሮጀክቶች እና ከከተማው ነዋሪ በተለያዩ መንገድ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለሚሰጡ አገልግሎቶች ፣ ለአቅርቦት ድጎማዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ቁጠባን መሰረት ያደረገ ስራ ላይ የሚውል ነው ብለዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.