.png)
የከተማው ካቢኔ በአራት ተቋማት አወቃቀር ላይ አፅድቆ በላከው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት በአቀረበው በደንብ ቁጥር 13/2016 መሰረት በረቂቅ ደንብ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል፡፡
የቱሪዝም ኮሚሽን ለብቻው ወጥቶ መደራጀትን አስመልክቶ አስፈላጊነቱ ላይ በአፅንኦት ተወያይቷል::
በዚህም መሠረት
1-ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፤
2-የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት ጋር እንዲወሀድ::
3 ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲወሃድ::
4-የከተማ ውበትና አረንጋዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት ተግባር ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ላይ ምክርቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.