
ከምክር ቤት አባላት እየተነሱ ያሉ ጥያዎች የህዝብን ጥቅም ማእከል የያደረጉ ናቸው ለዚህም የተከበረውን ምክር ቤት ማመስገን እወዳለው፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ህዝቡ ዋነኛው የሰላም ባለቤት እንደመሆኑ መጠን የተጀመረው ልማት በየትኛውም ጸረ-ሰላም ሀይል እንዲደናቀፍበት አይሻም ፡፡
በመሆኑም ከጸጥታ አካላት ጋር እጅና ጓንት በመሆን በመስራት ላይ የሚገኘውን የሰላም ሰራዊት በቁጥርም በጥራትም በብቃትም አሁን ካለው በላይ እንዲጠናከርና አቅም እንዲፈጥር ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
የሰላምና የጸጥታ ጉዳይ በከፍተኛ ትኩረት ሊሰራ የሚገባው ቀጣይና ዘላቂነቱን አስተማማኝ መሆን ያለበት ተከታታይ ጥረት የሚጠይቅ ተግባር በመሆኑ የከተማችን የጸረ-ሰላምና ወንጀለኞች መሸሸጊያ እንዳትሆን በምናለማው መሰረተ ልማት ዘመናዊ የሴኪዩሪቲ መሳሪያዎችን በመግጠምና በህዝቡና በጸጥታ ሃይሉ መካከል ያለውን ቅንጅት በማሳደግ ወንጀልን ከመከላከል አንጻር ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል፡፡
ከስደተኞች ጋር በተያያዘ የአገራችን ታሪክ ስደተኞችን በመቀበልና በማስተናገድ የሚታወቅና ከተማችንም አለማቀፉን የስደተኞች ህግጋት አክብራ እንደቤታቸው መኖር እንዲችሉ እድል ሰጥታለች፡፡
ይህ ማለት ግን በህገወጥ መንገድ በብሄራዊ ደህንነታችንና በከተማችን ሰላምና ሀገራዊ ጥቅማችን ላይ ክፍተት እንዲመጣ እድል መስጠት አይደለም፡፡ በከተማችን በሰነድና በሰነድ አልባ የሚኖሩ ስደተኞች በህገወጥ ወንጀሎች ላይ በተጨባጭ ተሰማርተው አግኝተናቸዋል፡፡
ከዚህም በላይ በሽብር ድርጊት ለመሰማራት ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ ሀይሎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ የሰላሙ ባለቤት እንደመሆኑ መጠን በጥቆማ እና የአካባቢውን ሰላም ነቅቶ በመጠበቅ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል፡፡
አገልግሎትን በተመለከተ የከተማችንን ነዋሪዎች እርካታን ከማረጋገጥ አንጻር አሁንም የሚቀሩን ነገሮች አሉ፡፡ በተለይ በመሬትልማት አስተዳደር አገልግሎትን ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግና ዲጂታል አገልግሎትን ከማሳደግ አንጻር የተጀማመሩት ስራዎች በጥሩ ጎን መታየት አለባቸው፡፡ አሁን ባለው ደረጃ 347 የሚሆኑ አገልግሎቶችን በክቡር ጠ/ሚኒስትራችን በተጀመረውን የመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመዝግጅታችንን በማጠናቀቅ ላይ ነን፡፡
በተለይ ዲጂታል አገልግሎቶችን ከማልማት አንጻር አገር በቀል ኮንትራክተሮችንና የዘርፉ አልሚዎችን አቅም በስፋት መጠቀም ላይ ትኩረት የምናደርግ ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል በተገልጋይና ከባለሞያዎች ጋር ተያይዞ ቴክኖሎጂውን በእኩል አቅም ተረድቶ ከመስራትና ከመገልገል አኳያ ያለውን የእውቀትና የክህሎት ችግር መፍታት ሌላኛው ውጤት ያገኘንበት ተግባር ነው፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.