በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ፋይናነ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ፋይናነስ ቢሮ ኃለፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በ3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ምላሽ፤-

👉የከተማችን ወጪ በየዓመቱ በዋናነት መነሻ የሚያደርገዉ ብድር እና እርዳታን በአማካይ ከወሰድን ከ2 በመቶ ያልበለጠ ሲሆን 98 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከከተማችን በጀት ከዉስጥ የሚመነጭ እና ወጪዎቹም በዋናነት የሚሸፍኑት ከዚሁ የዉስጥ ገቢ ግምት ዉስጥ ማድረግ ችለናል።

👉ከተማችን አገልግሎት ሰጪ በመሆኗ አገልግሎቱ በየዓመቱ ማደግ ስላለበት ከፍተኛ የሆነ የመደበኛ ወጪ ፍላጎት ያስከትላል፡፡ በተጨማሪም የተገልጋይ እርካታን ከማረጋገጥ አንፃር ተያይዞ የሪፎርም እና የዲጂታላይዝ ስራዎችን ለመስራት እና ተደራሽ ለማድረግም በቂ ግብዓት በማቅረብ የመደበኛ ወጪ ከፍ እንዲል የግድ ስለሆነ እየሰራን እንገኛለን፡፡

👉እንደ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት  50 እና 50 የነበረዉ በጀት በተወሰነ ደረጃ በመደበኛ ወጪም 50 በመቶ ደርሶ የነበረዉን በመቀልበስ ከተማ አስተዳደሩ በወሰደዉ ቁርጠኛ አቋም በዚህ በጀት ዓመት ከ70 በመቶ በላይ የካፒታል በጀትን ማድረስ መቻላችን አንዱ ማሰያችን ነዉ፡፡

👉ከ2010 እስከ 2013 የከተማዉን በጀት እድገት በአማካይ ስናይ ትልቁ ያደገዉ በ15 ፐርሰንት ፤ትልቁንም ብር ከወሰድን 7.8 ቢሊዮን ብር እድገቱ ነዉ፡፡በዚህም ዝቅተኛዉ 3.9 ቢሊዮን ከፍተኛዉ በአንድ ዓመት 7.68ቢ ሲሆን ከ2014 እስከ 2017 ዝቅተኛ ዓመታዊ ገቢ ያደገዉ በ40 በመቶ ሲሆን ከፍተኛዉ ደግሞ ከበፊቱ በ53 በመቶ ገቢያችን ማሳደግ ችለናል።

👉የ2017 በጀት ዓመት ከባለፈዉ ዓመት የ83 ቢሊዮን ብር እድገት ያለዉ ሲሆን ይህም ገቢን ለማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ ግብረ ኃይል አቋቁሞ በትኩረት የሰራበትና ትልቁ ዉጤት ሊሆን ችሏል፡፡

👉ለገቢ እድገታችን ሌላዉ ምክንያት በፊት ከነበረዉ የትንበያ ልማዳዊ አሰራር በመላቀቅ ከተማዋ ያላትን ገቢ የማመንጨት አቅም በጥናት በመለየት፤በቁጠባ በጀትን በመጠቀም፤በአሰራርና አደረጃጀት በማዘመን ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ተገቢዉን ምላሽ ከተማ አስተዳደሩ እየሰጠ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.