
በተለያዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶች ተሳታፊ የሆኑ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ በትኩረት መሰራቱ ተገለፀ ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት ዓመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል፡፡
አስፈጸሚ አካላትም ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋዉ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማን ማዕከል አርገው የሚኖሩ ስደተኞች በግድያ፣ በዘረፋ፣በህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውርና ህትመት ብሎም የማታለል ወንጀል ተሰማርተው የተገኙ ህገ ወጦችን ተከታትሎ የመያዝና ተጠያቂ የማድረግ እርምጃዎች ተወስደዋል ብለዋል።
የሀገር ህልውናን በሚጎዳ መልኩ ከፀረ-ሠላም ሀይሎች ጋር መረጃ የሚለዋወጡና ድጋፍ የሚሰጡ ህገ ወጥ ስደተኞችንም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማካሄድና የተጠያቂነት ስራ መሰራቱን ጨምረው አብራርተዋል።
በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች እና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራት በከተማዋ ሠላምን ማስፈን እንደተቻለ ያነሱት ኮሚሽነሩ ለመዲናዋ ሠላምና መረጋጋት ሚናውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.