
የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር በተለይ ዜጎችን በዘላቂነት በቋሚነት ለማሰማራት እንደ ከተማ አስተዳደራችን ባለፉት አመታት ስትራቴጂክ አስቀምጠን ወደስራ ገብተናል፡፡ አቶ ጥራቱ በየነ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
በዚህ በጀት ዓመት ለ366 ሺህ 44 ቋሚ የስራ እድል ፈጥረናል፡፡ ከዚህ ውስጥ ተደራጅተው ወደ አምራችነት ሊያሸጋግራቸው የሚችሉ 44 በመቶ በመደራጀት የተፈጠረ 163 ሺህ 700 ከተማችን ወጣቶች ተደራጅተው በከተማ ግብርና ፣በኢንዱስተሪ እና በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ ወደ ስራ የገቡ ናቸው ፡፡
እንደ ከተማ ግብርና ላይ በጣም ትኩረት አድርገን እየሰራን ነው በተለይ የከተማ ገብርና አሁን ካለው የኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ በቂ ገበያ በከተማችን ውስጥ ያለ በመሆኑ ስራ እድል የመፍጠር ስራችን እነዚህን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን እየሰራን እንገኛለን፡፡
ከገበያ ትስስር ከመፍጠር ጋር በተያያ እንደ ከተማ በምንሰራቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ በቀጥታ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራን ነው ያለነው በዚህም በመደበኛ ፕሮጀክትም በኮሪደር ስራችንም ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር እየተሰራ ነው ለምሳሌ በኮንስትራክሽን ቢሮ፣በውሃ፣ በመንገዶች እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በጀት የተያዘላቸውን ጨምሮ በዚህ በጀት ዓመት 14ሺ 398 ለሚሆኑ ኢንተር ፕራይዞች የገበያ ትስስር ፈጥረናል በዚህም 14 ቢሊዮን ብር የሚሆን ትስስር የተፈጠረበት ነው፡፡ ሌላው በኮሪደር ልማት በቋሚና በጊዜያዊ ከ100 ሺ በላይ የስራ እድል መፍጠር ችለናል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.