
በበጀት ዓመቱ የኮሙኒኬሽን ስራዎች በተመለከተ፤-
በበጀት አመቱ ከተማ አስተዳደሩ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚያዊ፤ በፖለቲካዊ እና የልማት ስራዎች ያከናውናቸውን ተግባራት አስመልክቶ የመረጃ ተደራሽነትን በማስፋት ውጤታማ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ስራዎችን ማከናወን ተችሏል፡፡
ዋና ዋና ከተማ አቀፍ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና ሀገራዊ ፋይዳ ያለቸው ፕሮጀክቶች ዙሪያ መልዕክቶችን በማዘጋጀት በዜና፣ በአጫጭር ፕሮግራሞች፣ በዶክመንተሪ፣ በተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፣ በኅትመቶች፣ በፕሬስ ሪሊዞችና ፓናል ውይይቶች ተደራሽ በማድረግ በከተማዋ የልማት አጀንዳዎች ሕዝባችን የላቀ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል።
ከተማችንን አስመልክቶ የሚሰራጩ ሚዛን የሳቱና የተዛቡ 172ዐ መረጃዎች በመለየት የመመከትና ሚዛን የማስያዝ ሥራዎችን በመስራት መረጃዎቹ እንዲታረሙ ማድረግ ተችሏል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.