
የከተማችንን የእህትማማች ግንኙነት ከማጠናከር አንፃር ፦
የጀርመኗ በላይብዚሽ ከተማ በአዲስ አበባ ከተማ ስም የአደባባይ ወካይ ሀዉልት ወይም መገለጫ ተሰርቷል፡፡
በደቡብ በኮሪያ የሴኡል ከተማ ስማርት ሲቲ 2024 115 አቻ ከተሞች መካከል በከተማ ለዉጥ ዘርፍ ቀዳሚ በመሆን በማሸነፍ ተሸላሚ መሆን ችላለች
አዲስ አበባ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች ኢንቨስትመንት ፎረም (Best Africa Smart Cities Award) አሸናፊ ከተማ ሆናለች፡፡
ከናሚቢያዋ ዋና ከተማ ዊንድሆክ (Windhock) እና ከቻይናዋ ሪጃው (Rizhao) ከተማ ጋር በዘላቂ ልማት፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በባህል፣ በንግድ፣በትምህርት እና ጤና መስኮች በትብብር ለመስራት ተችሎል ፡፡
በኮሪደር ልማት ስራችን ከልማቱ ማንም ወደ ኋላ ሳይቀር ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆን የተደረገበት የከተማችንን ደረጃ መሻሻል እና የተወዳዳሪነት አቅም የተፈጠርበት፣ የሥራ ባህል መሻሻል (24/7) ፣ የይቻላል አስተሳሰብ የዳበረበት ነዉ ፡፡
የከተማዋን ገጽታ መቀየር የተቻለበት ፣ የፕሮጀክት አመራርና የኮንትራት አስተዳደር አቅም ያገበት ፣ የባለድርሻ አካላት አቅም እየጎለበተ የመጣበት፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት የቅንጀት እና ትብብር ደረጃ በእጅጉ የተሻሻለበት ነዉ ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.