በበጀት ዓመቱ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎተ በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በበጀት ዓመቱ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎተ በተመለከተ፦

👉የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎተ ለማሻሻል 1ዐዐ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችና 15ዐ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች ተገስተዉ የትራንስፖርት ተደራሽነትን ማሻሻል ተችሏል፡፡

👉የብዙሃን ትራንስፖርት በቀን በአማካኝ በህዝብ ትራንስፖርት የሚጓጓዝ ህዝብ 3.79 ሚልየን ለማድረስ ታቅዶ ለ4.025 ሚሊየን አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

👉የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በሪፎርም በበጀት ዓመቱ ባለስልጣን መ/ቤቱ ካሉት 45 ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል 35ቱን በቴክሎጂ በሲስተም አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የተገልጋዮችን ፋይል በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአዲስ መልክ በማደራጀት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ ውጣ ውረዶችን በማስቀረትና የሚፈለጉ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡

👉ለዓመታት ቁጥጥርና ምዘና ሳይደረግባቸው የቆዩ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ እና የተሸከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ላይ በበጀት ዓመቱ ቁጥጥርና ምዘና በማድረግ ጉድለት የተገኘባቸው ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል፡፡

👉ለትራፊክ አደጋ የሚያጋልጡ (risk factors) የትራፊክ ደንብ ጥሰቶች ቁጥጥር በማጠናከር፤ የቁጥጥር ስርዓቱን በማዘመን አዲስ ሲስተም በማልማት በድምሩ 2.5 ሚሊየን የሚሆኑ ደንብ ተላላፊዎች ላይ የትራፊክ ቅጣት ተፈጽሟል፡፡

👉ከፓርኪንግ ስራ ጋር በተያያዘ ተቋሙ ያለማውን አዲስ ፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም ተግባራዊ በማድረግ 144 ማህበራት ወደ ስርዓት በማስገባት 310,000 በላይ ተሸክርካሪዎች በተዘረጋው ሲስተም እንዲያለፉ ተደርጓል፡፡

👉በአጠቃላይ በኮሪደር የለሙ የተሸከረካሪ ማቆሚያ ቦታዎች የካ ቁጥር 2 ጨምሮ ወደ አግልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.