
በበጀት ዓመቱ ጤናን በተመለከተ
በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጥ የወሊድ አገልግሎት ለ170,155 እናቶች በመስጠት ከእቅዳችን 94% ማሳካት ተችሏል::
የተመላላሽ ህክምና ተጠቃሚነት ቁጥርን በድግግሞሽ 16.6 ሚሊየን ጊዜ መስጠት ተችሏል፡፡
o ለ246,056 አስተኝቶ ህክምና ተገልጋዮች ተደራሽ በማድረግ ከእቅዳችን 117% ማከናወን ችለናል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ለማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ በማድረግ አምና ከነበረው 2.45 ሚሊየን አጠቃላይ የፕሮግራሙ የታቀፉ አባላት ቁጥር ዘንድሮ በእቅዳችን መሰረት 2.5 ሚሊየን ለማድረስ ተችሏል፡፡ በኮልፌና በንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ሁለት አጠቃላይ የሪፈራል ሆስፒታሎች ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡:
የጥሩነሽ ቤጅንግ፣ የራስ ደስታ፣ የዘውዲቱ ሆስፒታል እና ሚኒሊክ ሆስፒታል እየተሰራ ያለው ግዙፍ ማስፋፊያ በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን፡፡
ስምንት አዲስ ጤና ጣቢያዎች ግንባታቸው የተጠናቀቀና በቅርቡ ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በአራት ነባር ሆስፒታሎች እና ሌሎች ተጨማሪ ጤና ጣቢያዎች የተቋማቱን አቅም በሚያሳድግ መልኩ ሰፊ እድሳቶች ተሰርተዋል፡፡
የጤና መረጃ ስርዓታቸውን ሙሉ ለሙሉ ወረቀት አልባ ያደረጉ የጤና ተቋማት አምና ከነበሩት 40 ጤና ተቋማት ወደ 57 የጤና ጣቢያ ተቋማት በማሳደግ ችለናል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.