በበጀት ዓመቱ የትምህርት ዘርፍ በተመለከተ

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በበጀት ዓመቱ የትምህርት ዘርፍ በተመለከተ

👉የትምህርት ዘርፉ ዋና ትኩረት የነበረውን የትምህርት ተሣትፎና ፍትሐዊነት በማሳደግ በዕውቀትና በሥነ- ምግባር የታነፀ ትውልድን ለማፍራት በተሻሻለው ስርአተ ትምህርት መሰረት

👉በበጀት ዓመቱ የትምህርት አጠቃላይ ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ቅበላ ሥራችንን ከ1,159,684 ወደ 1,184,326 ለማድረስ ታቅዶ ክንውን 1,253,737 (105.86%) ማድረስ መቻሉ፤ይህም ከ 2016 የትምህርት ቅበላ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 98,129 ዕድገት አሳይቷል፡፡

👉የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረትም በሁሉም ት/ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎችን ቁጥር ከ 33,203 ወደ 33,604 ለማድረስ ታቅዶ 34,015 (101.22%) ማድረስ ተችሏል፡፡

👉ትምህርት ቤቶች ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች አመቺ እንዲሆኑ ለማድረግ የተማሪ መማሪያና የመምህሩ መምሪያ መፅሃፍትን በድምፅ በመቅረፅና አዘጋጅቶ በማሰራጨት 10,294 የዕይታ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች ተጠቃሚ በማድረግ ውጤታቸው እንዲሻሻል አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

👉የት/ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በሶስተኛው ዙር “ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ በተሰራው ሥራ በገንዘብ፤ በጉልበትና በዕውቀት በአጠቃላይ ከ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ የት/ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ለመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ተችሏል፡፡

👉ትውልድ ላይ ኢንቨስት እናድርግ በሚለው የመንግስት አቅጣጫ መሰረት በተማሪዎች ምገባ 840,585 በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ እንዲመገቡ የተደረገ ሲሆን የተማሪ ዩኒፎርም፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና የመምህራን ጋዋን ጨምሮ እንዲደርሳቸው ከማድረግ በተጨማሪ የተማሪ ውጤት ለማሻሻል እየሰራን ያለዉ ስራ ከፍተኛ ውጤት እያመጣ ይገኛል፡፡

👉በ2017 ትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ በማምጣት ወደ ቀጣይ ክፍል የተሸጋገሩ ተማሪዎችን ከነበረበት 94.3% ወደ 95% ለማድረስ ታቅዶ 95% (100% ) ማድረስ የተቻለ ሲሆን በተመሳሳይ የ8ኛ ክፍል ከተማ ዓቀፍ ፈተና ውጤት ከነበረበት 79% ወደ 82% ለማድረስ ታቅዶ 88.8% (108.3) ማድረስ ተችሏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.