.png)
ዛሬ ማለዳ በ11 ክፍለ ከተሞች ከ5 ቢለዬን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዉ የተገነቡ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ እና 1,155 የህፃናት መጫወቻ ማዕከላትን በጥቅሉ 1277 ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
ይህ ውሳኔያችን በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመገንባት ከከተማችን ሀብት መሬት እና በጀት፤ ከእኛ ከአመራሮች እና ከሰራተኛው ደግሞ ጉልበት እና ጊዜ እፍታውን ወስደን እንዲሁም ማህበረሰቡን በማስተባበር ለትውልዱ ቅድሚያ ስጥተን ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ገንብተናል ።
ባለፋት 3 ዓመታት ለስራ ቦታዎች እና ለመኖሪያ አካባቢዎች ጭምር ትኩረት በመስጠት በድምሩ 3,789 የህፃናት የመጫወቻ ማዕከላትን እና 1,530 የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ እነዚህ ደረጃዉን ጠብቀን የገነባናቸዉ መሰረተ ልማቶች 50 % ወጪያቸው የተሸፈነዉ በማህበረሰቡ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል።
በመጨረሻም፣ ለወጣቶችና ህጻናት የስፖርት ማዘውተሪያና መጫወቻ ማዕከላትን ለመገንባት ስናደርገው በነበረው ጥረት ሁሉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ላስተባበሩ አካላት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.