
የንቅናቄ ስራዎች የላቀ ድል ለማስመዝገብ ማስፈንጠሪያዎች በመሆናቸው በልዩ ትኩረት ሊከወኑ ይገባል !
በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በስራ ዕድል ፈጠራ ፣ በሌማት ቱሩፋት እና ልመናንና ተረጅነትን ከማስቀረት አኳያ ባለፈው ሳምንት በየክ/ከተማው የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም የጋራ ያደረጉ ሲሆን፤ በንቅናቄው ጅምር እንቅስቃሴዎች ላይ የነበሩ ጉድለቶች እንዲታረሙ ፣ ጥንካሬዎች ደግሞ እንዲጎለብቱ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ባስተላለፉት መልዕክት የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የሌማት ቱሩፋት እና ሌሎችም የንቅናቄ ስራዎች በቅርቡ በከተማ አቀፍ ግብረ ሀይሉ መገምገማቸውን አስታውሰው ጊዜና ጉልበትን በሚቆጥብ መልኩ በዛሬው ዕለት የተጀመረው በቴክኖሎጂ የታገዘ የግንኙነት አግባብም ስራዎችን ከስር ከስር እየገመገሙ ለመሄድ እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
አመራሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ስለሚመራ ስራዎች እንዳይንጠባጠቡ ማቀናጀትና በሱፐርቪዥን ማስደገፍ እንደሚገባው ያሳሰቡት አቶ ሞገስ በፓርቲያችንም ቀይ መስመር ተብሎ የተቀመጠውን የሀሰት ሪፖርት ፣ እንደ ቆሻሻ የመፀየፍ ባህልን ማጎልበት እንደሚገባም በአፅንዖት ገልፀዋል።
የሌማት ቱሩፋት ስራዎች በገበያ ማረጋጋቱ ላይም ትርጉም ያለው ውጤት ሊያመጡ ስለሚገባ በተለይም ለዘርፉ ዕምቅ አቅም ያላቸው የማስፋፊያ ክ/ከተሞች አንፀባራቂ ድል ለማስመዝገብ በልዩ ትኩረት ሊረባረቡ እንደሚገባ አቶ ሞገስ አስገንዝበዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ እና የክንፎች አመራሮች ፣ የወጣቶችና ስፖርት እንዲሁም የሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ አመራሮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ርብርብን ማጠናከር እንደሚገባቸው የጠቆሙት አቶ ሞገስ ለንቅናቄ ስራዎች የተቋቋሙ ግብረ ሀይሎችም የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ሁሉም የግብረ ሀይል አባላት ሀላፊነታቸውን በተናጠልም በቅንጅትም በቁርጠኝነት በመፈፀም ፣ ስራዎችን በየወቅቱ በመገምገም ውጤቶችን ይበልጥ ማላቅ እንደሚገባ አስረድተዋል።
ስራዎች በቴክኖሎጂ ታግዘው እየተከናወኑ መሆናቸው የሀሰት ሪፖርትን ለማስቀረትም ተጨማሪ አቅም መፍጠራቸውን ያስረዱት አቶ ጥራቱ የተፈጠሩ የስራ ዕድሎችን እና የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን ሙሉ መረጃ አደራጅቶ መያዝ ሊጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።
ባለፈው ሳምንት ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት በኩል ከመቶ በላይ ዕቅዳቸውን ያከናወኑ እንዳሉ ሁሉ ምንም ያልጀመሩ መኖራቸው ፣ የቴክኒካል ክህሎት ስልጠናዎች ላይም የአፈፃፀም ልዩነቶች መኖራቸው፣ በስራ ዕድል ፈጠራውም ከሚጠበቀው አንፃር ክፍተቶች መኖራቸው በቀረበው ሳምንታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተመላክቷል።
የከተማ ግብርና ስራዎችን በተቀናጀ አግባብ ወደ ስራ ከማስገባት አንፃር አበረታች ውጤቶች ቢኖሩም ስራዎችን አስተሳስሮ መምራት ላይ የነበሩ ውስንነቶችም ሊታረም እንደሚገባ ተጠቁሟል ::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.