
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ የሰላም፣ የፀጥታ እና አለምአቀፍ አመራር መድረክ መክፈቻ ወቅት ባደረጉት ንግግር ስኬታማ ትብብርን ለማስቻል አፀፋዊ መተማመንን የሚያሳድጉ አለምአቀፍ ተቋማት የመኖርን አጣዳፊነት አንስተዋል።
አለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት የጋራ ደኅንነትን እና ሁሉን አካታች ብልጽግናን ለማምጣት ይረዳ ዘንድ የውሳኔ አሰጣጥ መዋቅራቸው ምሉዕነት ባለው መልክ የሚሻሻልበትን ሁኔታም አፅንኦት ሰጥተው አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በይፋ ወደ ብሪክስ የተቀላቀለችው በ2015 ዓ.ም ሲሆን ኢኮኖሚያዊ ወዳጅነት ብቻ ሳይሆን ፍትኃዊ የሆነ፣ እኩልነት የሚሰፍንበት ብዝኃ ዋልታዊ አለምን ለመፍጠር ከሚተጉ ሀገራት ጋር በእኩል ደረጃ የተሰለፈችበት ስብስብ ነው። እንደ ብሪክስ አባልነቷ ኢትዮጵያ እነዚህ ጥረቶች እንዲሳኩ በተለይም በአለምአቀፍ ውሳኔ ሰጪ መድረኮች ለአዳዲስ ገበያዎች እና በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ሰፋ ያለ ውክልና በሚገኝበት ሁኔታ ላይ በንቃት አስተዋፅኦ ታደርጋለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የብሪክስን እያደገ የመጣ ተፅዕኖ ሲገልጹም የሚከተለውን ብለዋል።
”ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለአለምአቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል። አዳዲስ አባላት በመጨመራቸውም የጋራ ድምፃችን የበለጠ ይጠናከራል። የጋራ አላማችን የበለጠ ይጠራል። አቅማችንም ይሰፋል።”
#PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.