
ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገናል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች (all weather strategic partners) ባለፉት ሰባት ዓመታት ትብብራችን ጉልህ ፍሬዎችን አፍርቷል። ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ ትኩረታችን እንዳለ ሆኖ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጠናከርና እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ሎጂስቲክስ እና ንጹሕ የኃይል ምንጮች ልማት ላይ ያለንን ዕምቅ ዐቅም ለመመልከትም ችለናል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.