የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር እንኳን ለመደበኛ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር እንኳን ለመደበኛ ጉባኤያችሁ አደረሳችሁ ፡፡ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መደራጀት ሃይል ነው። የመደራጀት ዋና ግቡ  በተናጠልና በተበታተነ መንገድ ማሳካት የማንችለውን በህብረት በቀላሉ ከግብ ማድረስ ማስቻሉ ነው።
ወጣቶች ተደራጅታችሁ መንቀሳቀሳችሁ  ለተጠቃሚነታችሁ እና በሁሉም ዘርፍ ያላችሁን ተሳትፎ ለማጐልበት ወሳኝ ነው፡፡ 

ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናት!

የምንሰራው ከምንም በላይ ለወጣቶች እና ለነገ ትዉልድ ተጠቃሚነት ነው። የከተማችን አመራሮች 70 በመቶ ያህሉ ወጣቶች ናቸው። የወጣቶችን ስብዕና መገንቢያ እና የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በስፋት እየሰራን ያለነዉም በአካል እና ስነልቦና የጎለበታችሁ ብቁ ዜጋ ትሆኑ ዘንድ ነዉ።

የከተማችን ወጣቶች በልማት ላይ ያላችሁ ተሳትፎ በተለይ በበጎ አድራጎት ስራ ያከናወናችሁት ስራ እጅግ ያስመሰግናችኋልና በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። 
ጉባኤያችሁ የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞቴ ነው፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.