
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !! እንኳን ደስ አላችሁ!!
ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን አጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡
ከተማችንን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራ እንገኛለን፡፡
ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦
ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ፣
ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ አደባባይ፣
ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ፣
የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣
ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ፣
ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ፣
ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን፣
ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.