በመዲናዋ ተገንብተዉ የተጠናቀቁ ከ15,960 በላ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናዋ ተገንብተዉ የተጠናቀቁ ከ15,960 በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀዉ ከነገዉ እለት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ገለፁ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በ2017 በጀት ዓመት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው የጎላ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎችን በማቀድና ተግባራዊ በማድረግ ከ15 ,960 በላይ የተለያዩ ትልልቅ ፕሮጄክቶች ከነገ እሁድ ሰኔ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተመርቀዉ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ተናግረዋል፡፡ 

ለአገልግሎት ክፍት ከሚሆኑት እና ከሚመረቁትፕሮጀክቶች መካከል የመንገድ፣ የውሃ፣ የቤቶች ልማት ፣ የመስሪያ ቦታዎች፣ የወጣቶች ስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳዎች፣ በአረንጓረዴ ልማት የተሰሩ  እና ሌሎች ለህብረተሰቡ ፋዳቸው ጉልህ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ያካተቱ ናቸው  ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በ91 ቢሊዮን ብር ወጪ በመንግስት እና በ4 ቢሊየን ብር ወጪ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ ሲሆን ፤ የተጠቀሰው በጀት ብቻ ሳይሆን ሌሎች በሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችም በፈጣን ክትትል ሥራው ውስጥ እንዳሉ  ወ/ሮ እናት ዓለም መለሰ በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል፡፡  

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ከተያዘለት በጀት ውስጥ 71 በመቶ የሚሆነዉን  ለካፒታል ፕሮጀክት ግንባታ እና ለድህነት ቅነሳ ፕሮግራም እንዲውል በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን፣ ገልጸው፣ ለትራንስፖርት ለዳቦ ፍብሪካ ድጎማ፣ ለባሶች ግዥ፣ ለተማሪዎች ምገባ፣ ለጤና መድህን ፕሮግራሞች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም  የቢሮው ኃላፊ አስረድተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለወጣቶች ስራ እድል በሰጠዉ ትኩረት ከ366ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.