“የሚሰሩ እጆች ወግ”

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“የሚሰሩ እጆች ወግ”

ዛሬ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ከአዲስ  ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በመሆን ለአንድ ዓመት የሚቆይ “የሚሰሩ እጆች ወግ” የሚል የስራ ባህልን ለማዳበር እና የስራ ክቡርነት ግንዛቤን ለማሳደግ የሚረዳ  የቴሌቭዥን ፕሮግራም  ከስራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በመሆን ይፋ አድርጓል።

ስንፍናን መጠየፍ ፣ በትጋት መስራት፣ የሚሰሩ እጆችን መደገፍ እና ማክበር የሰለጠነ ማህበረሰብ መገለጫዎች ናቸዉ።

ኢትዮጵያ የምትቀየረው  በመስራት  ነው።  የዜጎችን ህይወት መቀየር  የሀገር ክብር ነው። ስንፍናን በመጠየፍ እና የሚሰሩ እጆችን በማክበር ረገድ  ከንግግር ያለፈ ውጤታማ ተግባር  ከሁላችንም ይጠበቃል።

ሀገራችን ስንፍናን እና ልመናን መፀየፍ  ይገባታል። ከቤተሰብ ጀምሮ  የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች  እና ተጽእኖ ፈጣሪዎች በአስተምህሮታችሁ  ህዝባችን ተግቶ እንዲሰራ፣ ስራ አጥ ስራን ማማረጥ እዲተዉ፣ ስንፍናን አብዝቶ እንዲፀየፍ በድፍረት “ያልሰራ አይብላ” በማለት ማስተማር ይጠበቅባቸዋል።

ወጣቶች የጊዜን ውድነት ተረድተዉ  ጊዜያችዉ በማይረባ ነገር እንዳይባክን  ማገዝ፣ ሁኔታዎችን ማመቻቸት  እና ተስፋ ሰንቀዉ  እንዲሰሩ ማበረታት ከሁላችንም የሚጠበቅ ሀላፊነት ነዉ።
  
ይህንን የቴሌቪዥን  ፕሮግራም ስራ ፈጣሪዎች፣  ኢንዱስትሪዎች  እንዲሁም መላው ማህበረሰብ  ከልብ እንሳተፋበት እና እንዲጠቀምበት መልዕክቴን እያስተላለፍኩ፣ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ እና አዲስ  ሚዲያ ኔትወርክ ግንዛቤ የሚያሻሽል እና የሚያበረታታ  የቴሌቭዥን ፕሮግራም ስላዘጋጁ አመሰግናለሁ። 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.