የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በአራት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ፤

1ኛ:- የከተማዋን ፈጣን ለዉጥ  ታሳቢ በማድረግ፣ ወጪን ለመቀነስ ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ወጤታማነትን ለማሳደግ እንዲረዳ ተጠንቶ የቀረበዉ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የማሻሽያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለምክር ቤት እንዲቀርብ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡ 

በዚህም መሠረት 
1..ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፤ 

2..የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት ጋር እንዲወUድ፤ 
3.. ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲወUድ 

4..የከተማ ውበትና አረንጋዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት  ተግባር ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ተደርገዉ ለምክቤት እንዲቀርብ ወስኖል።

2ኛ:-ለአስተዳደራዊ አመቺነት ፣ ለአገልግሎት ተደራሽነት እና ወጪን ለመቀነስ እንዲያግዝ በፕላን ልማት ቢሮ ተጠንቶ በቀረበዉ የሶስት የወረዳዎች አስተዳደር ወሰን ማሻሻል ጥናት ላይ ተወያይቶ አገልግሎት ተደራሽነትን እና ወደፊት በከተማዋ የሚመጣውን ልማት ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ  የቀረበውን ማሻሻያ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

3ኛ:-በጤና ቢሮ በኩል ተጠንቶ በቀረበዉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት ክፍያ መጠን ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡

4ኛ. አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጀክቶች ላይ የቀረበ የመሬት ልማት ጥያቄ ላይ በመወያየት አፅድቋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.