
የ2018 በጀት ትኩረትና የቀጣይ ዓመት ሀገራዊ ዕድገትን በተመለከተ
አጠቃላይ በጀታችን ለድህነት ቅነሳ ትኩረት ያደረገ ነው፤ ከዚያ የተረፈው ለዕዳ ክፍያ እና ድጎማ ለሚያስፈልጋቸው የሚውል ነው። አብዛኛው ገንዘባችን ድጎማ፣ ዕዳ ክፍያና መሰል ጉዳዮችን ስለሚያካትት የካፒታል በጀታችን ዕድገት ቢኖረውም ውስን ነው። በአንድ በኩል የኑሮ ውድ ሆነ ደሞዝ ችግር ሆነ እያልን እሱን ሳንመልስ በውስን ገቢ ያገኘውን ገቢ በሙሉ ልማት ላይ ካዋልን ችግሩ ስለሚባባስ ያንን እያስታረቁ መሄድ ያስፈልጋል። የእኛ ዕድገት መታየት ያለበት ስንት ኩንታል እንደጨመርን ነው። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም እንደነበረው የቁጥር ሳይሆን ጥራት ያለው ዕድገት እያስመዘገበች ነው። ይህም የሚታይ ዕድገት ነው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት የበለጠ ትልቅ ውጤት ያስመዘግባል። ያ እንዲሆን ግን ሁሉም ዝቅ ብሎ አፈር እየነካ በትጋት በመስራት፣ ህዝብን በማስተባበር፣ ሌብነትን በመቀነስ፣ በውጤት ማመን፣ ጀምሮ በመጨረስ፣ የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሁላችንም እምነት በማድረግ ልማትና ዕድገት ይመጣል። ኢትዮጵያ እያደገች ነው፤ ኢትዮጵያ እያንሰራራች ነው፤ ኢትዮጵያ አቧራዋንና እዳዋን እያራገፈች ነው። የበለፀጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናስረክባለን።
#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.