#የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

#የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia

ኢንዱስትሪን በተመለከተ

በኢንዱስትሪ ዘርፍ ዘንድሮ 12 በመቶ ገደማ ዕደገት ለማምጣት ታቅዶ እየተሰራ ነው። ኢትዮጵያ ታመርት በሚል ንቅናቄ በጣም ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል። የኢትዮጵያ ታምርት የማምረት አቅም አምና 59 በመቶ ነበር የደረሰው፤ ዘንድሮ 65 በመቶ ደርሷል። ይህም የፋብሪካዎችን የማምረት አጠቃቀም በማሳደግ ነው። በዚህ ዓመት የኢንዱስትሪው የኃይል ፍላጎት በ40 በመቶ ደርሷል። ይህ ትልቅ ዕድገት ነው፤ የሲሚንቶ ምርት ከፍ ብሏል፤ በብረት ውጤቶች 18 በመቶ ዕድገት ተመዝግቧል። ብረት የማምረት አቅም ገንብታለች። የብራት ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ ማሟላት የሚያስችሉ ስራዎች ተጀምረዋል። የመስታወት ፋብርካ በዓመት 600 ሺህ ቶን ገደማ የሚያመርት እየገነባ ይገኛል። የፋብሪካው ስራ በማንኛውም መስፈርት አድናቂ ነው። በሚቀጥለው ታህሳስ ወይም ጥር ላይ ይጠናቀቃል። የሶላር ምርት ፓናል ምርት የሚያመርት ፋብርካዎችም እየተገነቡ ነው በቅርቡ ይመረቃሉ፤ ኢንዱስትሪውን ለማነቃቃት እየሰራን ነው።

ማዕድን ማዳበሪያ እና የጋዝ ምርትን በተመለከተ

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የማዕድን አቅም ያላት ሀገር ናት፤ በአፍሪካ ውስጥ ትላልቅ የማዕድን አቅም ካላቸው ሀገራት አንዷ ናት፤ እስካሁን የትክረት የአመራር፣ የዕይታ ማነስ ስለነበረ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ማገዝ ይችል ነበር። አሁን እያነቃቃነው ነው፤ ወርቅ ባለፈው ዓመት በዚህ ዓመት 37 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገነዋል። 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኤክስፖርት ዓመት ያገኘነውም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን ስለሰራን ነው። ይህ በየትኛውም ዘመን ያልነበረ ስኬተ ነው። ሌላው ጋዝ ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዝ ላይ የሚሰማሩ ኩባንያወች ፈቃድ አውጥተው ወደ ተጨባጭ ስራ አይገቡም ነበር። ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት በቅርቡ ለገበያ ማቅረብ ትጀምራለች። በዚህም ሰርቶ አዳሪ እንጂ አውርቶ አዳሪ አለመሆናችንንም በተከታታይ እያሳየን እንቀጥላለን። የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፤ ከ40 ወራት በኋላም ተጠናቅቆ ስራ ይጀምራል።

የአገልግሎት ዘርፉን በተመለከተ

የአገልግሎት ዘርፍ 8 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ታቅዶ እየተሰራ ነው። ቱሪዝም፣ ትራንስፖርት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ የንግድ አገልግሎቶችን እና ቴክኖሎጂን ያካትታል። አገልግሎት ዘርፍ በተቀናጀ መንገድ ከተሰራበት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመሸከም ያለው ጉልበት ከፍትኛ ነው። ዘንድሮ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ኹነቶች ተስተናግደዋል። 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የውጭ ጎብኝዎች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። የኮሪደር ልማቱ፣ የምስህብ ስፍራዎች ግንባታ፣ አንድነት ፓርክ፣ ብሔራዊ ቤተመንግስት፣ ሳይንስ ሙዚየም ወዳጅነት ፓርክ ብቻ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች ጎብኝተውታል። ግማሽ ቢሊዮን ብር ገቢ አስገኝቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት 13 አዳዲስ አውሮፕላን ገዝቷል፤ ስድስት አዳዲስ መዳረሻዎችን ጨምሯል፤ ከ19 ሚሊዮን በላይ መንገደኘሞችን አጓጉዟል፤ የባቡር አገልግሎትም ወጪና ገቢ ንግድ ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው።

የፋይናንስ ዘርፉን በተመለከተ

የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርሙም በዚህ ዓመት አዎንታዊና ጤናማ ዕድገት አስመዝግቧል። የፋይናንስ የሞባይል መኒ 55 ሚሊዮን ደርሷል፤ የቨርቸኡዋል ግብይት በከፍተኛ መጠን እያደገ ነው። የዲጅታል ግብይት 12 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፡ ከጥሬ ገንዘብ ግብይቱም ከፍተኛ ብልጫ አለው። 24 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በቨርቹዋል ብድር ተደራሽ ተደርጓል። በአጠቃላይ በዓመቱ የታቀደው 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮፐኖሚ ዕድገት እንደሚሳካ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን በአገልግሎትና ሌሎችም ዘርፎች የተገኙ አመላካች ውጤቶች አመላካች ናቸው።

የወጪ ንግድ ሪፎርሙ ስኬትን በተመለከተ

በዚህ ዓመት ከወጪ ንግድ 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት ያሳካነው 8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ አሳክተናል፤ ይህም ከታቀደው 3 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ ነው፤ ከአምናው ከእጥፍ በላይ ነው።

ይህም የሪፎርሙ ስኬት፣ ከሬሚታንስ 7 ቢሊዮን ዶላር፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 4 ቢሊዮን ዶላር፣ ከአገልግሎት 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል።

አምና የውጭ ምንዛሬ ማግኛ መንገዶችን ከብድርና እርዳታ ውጭ ያሉትን ተጠቅመን ያገኘነው 24 ቢሊዮን ዶላር ነበር፤ ዘንድሮ 32 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝተናል። ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤት ማሳያ ነው።

ዕዳን ተመለከተ

በዚህ ዓመት 92 ቢሊዮን ብር ዕዳ ከፍለናል። ባለፉት ሰባት ዓመታት አንድም የንግድ ብድር አልተወሰደም። ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል። የዕዳ ሽግሽጉ ትናንት በፈረንሳይ የመጨረሻውን ስምምነት ገንዘብ ሚኒስቴር ተፈራርሟል። በዚህም 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ከዚህ ቀደም በነበሩት መንግስታት የተበደሩትን ዕዳ በማሸጋሸግ የኢትዮጵያን የዕዳ ቀንበር ማንሳት ችለናል።

ገቢን በተመለከተ

ዘንድሮ 900 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን አጠቃላይ ወጪያችን ደግሞ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ነው። የ300 ሚሊዮን ብር ልዩነት አለው። ገቢው ከአጠቃላይ ጥቅል ምርት አንጻር ምጣኔ በጣም ዝቅተኛ ነው። 46 ሺህ የሚጠጉ የታክስ ተመዝጋቢዎች ግብር እየከፈሉ አይደለም። ከፊሉ የኪሳራ ሪፖርት በማቅረብ፣ ከፊሉ ገቢና ወጪው ተመጣጣኝ ነው። ትርፍ የለኝም በማለት ከፊሉ ደግሞ ሪፖርት የማያቀርብ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ንግድ ፈቃድ ከወሰዱት መካከል ግብር እየከፈሉ ያሉት 37 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው። ከእነዚህም የሚሰበሰበው ገቢ ከአጠቃላዩ 60 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው። 40 በመቶውን ገቢ ከተለያዩ ምንጮች ነው የምናገኘው። በመሆኑም ዘንድሮ 37 በመቶ ብቻ የሆነውን የግብር ከፋይ ቁጥር 50 በመቶ እንኳን ማድረስ ከተቻለ ከታክስ የሚሰበሰበው ገቢ ይጨምራል። የታክስ አስተዳደራችንን ችግር ለማስተካከል ሪፎርም እየተደረገ ነው፤ ግብር ስወራን ማስቀረት አለብን። ኢ-መደበኛ የደረሰኝ ጉዳዮችን ማስተካከል አለብን። ግብር አከፋፈልን ዲጅታላይዝ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትም ውጤት እያመጡ ነው። ግብር ከፋዮች በታማኝነት ግብር መክፈል ካልቻሉ መንገድ፣ ውሃ፣ ትምህርት በጥቅሉ ሀገር የለም ማለት ነው። ይህን ታሳቢ በማድረግም የንግዱ ማህበረሰብ ግብራቸውን በታማኝነት ሊከፍሉ ይገባል።

የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበትን በተመለከተ

መንግስት ከብሔራዊ ባንክ ዓመቱን ሙሉ ብድር ሳይወሰድ ዓመቱን ማጠናቀቁ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል። የፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲ፣ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ፣ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ከፍተኛ ድጎማ መደረጉ፣ ምርትንና ገበያን በቀጥታ ማገናኘት መቻሉ ትልቅ ውጤት እንዲመጣ አስችለዋል። ምርታማነትን ማሳደግ የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ዋነኛው መፍትሔ ነው። የዋጋ ግሽበቱ ምጣኔ አምና ከነረበት 22 ነጥብ 8 በመቶ ዘንድሮ ወደ 14 ነጥብ 4 በመቶ ወርዷል። የዋጋ ግሽበቱ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ላይ ከፍትኛ ጫና እንዳያሳድር 350 ቢሊዮን ብር ድጎማ ተደርጓል። የዋጋ ግሽበቱ ከሁለት አሃዝ ወደ ነጠላ አሃዝ መውረድ አለበት። የዋጋ ግሽበትን ከፍላጎት ጋር ማማጣም የሚቻለው የእያንዳንዱን ሰው ገቢ ማሳደግ ሲቻል በመሆኑ አጠቃላይ ሀገራዊ እድገትን ማረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው። መፍትሔውም ፈተናዎችን በጋራ ተቋቁሞ መስራት ነው።

የመንገድ መሰረተ ልማትን በተመለከተ

የኢትዮጵያ የመንድ ሽፋን 175 ሺህ ኪሎሜትር ደርሷል። 1 ነጥብ 5 ትርሊዮን ብር የሚጠይቁ 300 ፕሮጀክቶች ጸድቀዋል። ውል በመፈራረም በተለያየ የስራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 169 ፕሮጀክቶች ከ11 ሺህ ኪሎሜትር በላይ መንገድ በአሁኑ ወቅት እየተገነባ ነው። በዚህ ዓመት ከ1 ሺህ ኪሎሜትር በላይ መንገድ ይመረቃል። 17 ሺህ ኪሎሜትር መንገድ የከባድና መካከለኛ ጥገና እየተደረገ ነው። በአጠቃላይ መንገድ 28 ሺህ ኪሎሜትር በጥገና እና በአዲስ እየተገነባ ነው። የመንገድ መሰረተ ልማት ሽፋንን የማሳደግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ህዳሴን ግድብን በሚመለከት

ህዳሴ ግድብ አልቋል። ህዳሴን እናስመርቃለን፤ ከመመረቁ በፊት ብንረብሽ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፤ ግን እናስመረቀዋለን። ክረምቱ ሲያልቅ እናስመረቀዋለን። ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለኝ መልዕክት ለግብፅና ለሱዳን ህዳሴ በረከት ነው። የሚመጣው ልማትና ኢነርጂ ለሁሉም ሀገራት የሚተርፍ ነው። ይግብፅ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ አልቀነሰም። ኢትዮጵያ እስከበለጸገችና እስካደገች ድረስ የግብፅ እና የሱዳን ወንድሞቻችንን ጉዳት አንፈልግም። ኢነርጂውንና ውሃውን በጋራ እንጠቀማለን፤ ልማትና እድገትም ይመጣል። ኢትዮጵያ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ለመነጋገር፤ ለመደራደርና፤ ለመስራት አሁንም ዝግጁ ናት። ለግብፅና ለሱዳን እንዲሁም ለተፋሰሱ ሀገራት መንግታት በሙሉ መስከረም ላይ ህዳሴን ስናስመርቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በይፋ እንጋብዛለን።

የመኖሪያ ቤትን በተመለከተ

የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በመንግስት፣ በግል፣ በመንግስትና በግል ትብብር እየሰራን ነው። ይህ አሰራር ከዚህ ቀደም አልነበረም። በዚህም ባለፉት አመስት ዓመታት 1 ሚሊዮን ገደማ ቤቶች ተገንብተዋል። አሁንም ከ265 ሺህ በላይ ቤቶች እየተገነቡ ነው። አሁንም የተጀመረው ስራ የሚናቅ አይደለም። በክረምት በጎ ፈቃድ ከ100 ሺህ ያላነሰ ቤት አድርሰናል። በገጠርም ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን ለመገንባት የገጠር ኮሪደር ልማት ጀምረናል። በከተማም በገጠርም የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሻሻል የጋራ ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.