የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ስብሰባ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ

ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ያስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው፤ በስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት፣ በወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል ሊገለፅ የሚችል ነው። ሁለተኛው ለግሉ ዘርፍ የስራ አካባቢው ምቹ አልነበረም። ሶስተኛው ምርታማነት ነው። በግብርናም በኢንዱስትሪም ምርታማነታችን ውስን ነበር። ይህም በርካታ ተግዳሮቶች እነዲስተናገዱ አድርጓል። አራተኛው ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሁኔታን አልፈጠርንም። እነዚህን ጉዳዮች ጨክነን በመፍታት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱን መፍታት እንችላለን ብለን ነው ወደ ተግባር የገባነው።

ግብርናን በተመለከተ

ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋለታ ነው። የወጪ ንግድ ገቢያችን ዋልታም ነው። በርካታ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚሳተፍበት ነው። ይህም ትልቅ ስፍራ እንዲሰጠው ያደርጋል። ግብርና ቢዝህ ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንዲያመጣ ነው የታቀደው። የግብርናው ዘርፍ ከሌሎች ዘርፎች ልዩ ትኩረት ያገኘው ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ማግኘት አለባት፤ አምርታ መብላት ያልቻለች ሀገር ብሔራዊ ጥቀሞቿን ለማረጋገጥ ትቸገራለች በሚል የምግብ ሉዓላዊነትነ ለማረጋገጥ ግብ ይዘን ሰርትናል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት 27 ሚሊዮን በሴፍቲኔት የተያዙ ዜጎች ነበሩ፤ እነዚህን ከሴፍቲኔት ለማሸጋገር ሲሰራ ቆይቷል፤  በዚህም ለረጅክም ዘመናት በሴፍቲኔት ሲተዳደሩ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ወደ መተዳደር  ተሸጋግረዋል። 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ነጻ ወጥተዋል። ይህ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ማሳያ ስለሆነ ኩራት ሊሰማን ይገባል። ቀሪው ከ4 ሚሊዮን ያላነሰ ተረጂም ነጻ በማውጣት ኢትዮጵየን ሙሉ ለሙሉ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች ሀገር ማድረግ አለብን። ለዚህም ሰፊ የሚታረስ መሬት አለን። 

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.