
እንኳን ደስ አላችሁ! ከአንጋፋው ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተመረቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።
ውድ ተመራቂዎች፤ የትምህርት ዘርፍ ተመራቂ እንደመሆናችሁ መጠን ትምህርት ትውልድን የሚቀርጽና የሚያንጽ መሳሪያ መሆኑን፣ መማር ደግሞ የአስተሳሰብ እና የአሰራር ለውጥ ማምጣት የሚስችል እንዲሁም የትምህርት ባለሞያነት ትውልድን በማነጽ ሃገርን የመገንባት የማይተካ ታላቅ ሃላፊነት ስለሆነ ስራ ላይ ስትሰማሩ ለአፍታም ሳትዘነጉ ለዉጤታማነቱ ልትተጉ ይገባል።
ተመራቂ ተማሪዎቻችን ወጣቶች ናቸሁ፤ መጪው ጊዜ ደግሞ የወጣቶች ነው። ከዛሬው የተሻለ ብሩህ ተስፋ ይጠብቃችኋል። ለሚጠብቃችሁ ብሩህ ዘመን የተማራችሁትን ወደተግባር መለወጥ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ተማሩ፤ እየተለወጠ ላለዉ ነገ ራሳችሁን ይበልጥ አዘጋጁ።
የስራ ዘመናችሁ ስኬታማ እንዲሆን ከልቤ እመኛለሁ !
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይባርክ
ከንቲባ አዳንች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.