"ለዘመናት ማህበረሰቡ ሲጠይቃቸው የነበሩ የመልካ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ለዘመናት ማህበረሰቡ ሲጠይቃቸው የነበሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎችን የመለሱ ተጨባጭ ስራዎች መሰራታቸውን በተጨባጭ አረጋግጠናል፡፡" የዉይይቱ ተሳታፊዎች

"አገልጋይነት፤የህሊና እርካታ የስብዕና አክሊል ነዉ!" በሚል መሪ ቃል ከነዋሪዎች ጋር ዉይይት ተካሄደ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ከፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት አስተባባሪነት በአገልጋይ ፕሮግራም እና እንጠያየቅ መድረክ የተነሱ የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ላይ የተሰጡ ተግባራዊ ምላሽ ዙርያ ከነዋሪዎች ጋር ዉይይት ተካሄዷል፡፡

በመድረኩ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፣ የክፍለ ከተማው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ ፣ የክ/ከተማው የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ንጋቱ ፣ የክ/ከተማው ከፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ተዋበ ፣ የክ/ከተማዉ አጠቃላይ አመራርሮች፣ የ12ቱም ወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፣ የወረዳ የዘርፉ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የምክርቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ከ12 ቱም ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረብ ክፍሎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

በመድረኩ የክፍለ ከተማው ማህበረሰብ በተለያዩ አግባቦች ሲያነሷቸው የቆዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተፈቱበትን መንገድ የሚያሳይ አጭር ዶክመንተሪ ቀርቦ ሰፊ፤ግልፅ እና ጥልቅ ዉይይት ተደርጓል፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀናን ጨምሮ የሚመለከታቸው ሴክተር ኃላፊዎች የጤና ጣቢያና የትምህርት ቤቶች ማስፋፊያ ፣ የጎርፍ አደጋ መከላከል ስራዎች ፣ የመሰረተ ልማት ስራዎች በስፋት ቢሰሩ የሚሉና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዉ በበኩላቸዉ በበጀት ዓመቱ "አቃቂ በለውጥና ውጤት ጎዳና" በሚል መሪ ቃል ወደ ስራ በመግባት በርካታ ውጤታማ ስራዎችን መስራት መቻሉን አስታዉሰዉ በተለይም ለበርካታ ዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

አያይዘዉም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እና ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር ፣ ብልሹ አሰራርና ሌብነት ለመከላከልና ፈጣን አገልግሎ ለመስጠት የያስችሉ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማዘመን እንዲሁም የሪፎርም ስራዎችን በስፋት በመስራት በራካታ ዉጤቶች መመዝገባቸዉን አመላክተዋል፡፡

አሁንም ቀሪ ስራዎች መኖራቸውንና ይህንንም ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ በስኬት ለማጠናቀቅ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዉ ለዚህም የእንጠያየቅ መድረኮች የማህበረሰቡ ድምፅ የሚሰማባቸው በመሆኑ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የክፍለ ከተማው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ በበኩላቸዉ መድረኩ በዋናነት ያስፈለገው በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎችን የጋራ ለማድረግና ያሉ ክፍተቶችን ከማህበረሰቡ ጋር በመለየት በቀጣይ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለዉም አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ የማህበረሰብ ጥያቄዎች የመለሱ በርካታ ስራዎችን መስራት መቻሉንና ለአብነትም ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ስራዎች ፣ የኑሮ ማረጋጋት ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች መሰራት መቻላቸውን ወ/ሮ ዉቢት ዩሃንስ በማብራሪያቸዉ አመላክተዋል፡፡

በቀጣይ አስተዳደሩ ከማህበረሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት የሚሰራ መሆኑንና ለዚህም ነዋሪው የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት የክፍለ ከተማውን የልማት ስራ የበለጠ ስኬታማነቱን ሊያረጋገጥ እንደሚገባ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም የዉይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ዉይይቱ ነፃ እና ዲሞክራሲያዊ ነፃነት የታየበት፤ በክፍለ ከተማው የተሰሩ የልማት ስራዎች የጋራ ስኬቶች መሆናቸዉ የበለጠ መነሳሳት የተፈጠረበት መሆኑን ጠቅሰዉ ለዘመናት ማህበረሰቡ ሲጠይቃቸው የነበሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎችን የመለሱ ተጨባጭ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.