
“ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል!” በሚል መሪ ቃል በየደረጃው ሲካሄድ የነበረው የመምህራን ውይይት የማጠቃለያ መድረክ አድርገናል::
መድረኩ ለሀገር ግንባታ መምህራን ያላቸውን ታላቅ ሚና በመረዳት በሀገራዊ ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ እንዲሁም ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን እና ሃሳቦችን በማዳመጥ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው::
መምህራንና ቤተሰቦቻቸው በነፃ የሚታከሙበት ሆስፒታል ግንባታን ጨምሮ ሌሎች መምህራኑ ያነሷቸውን ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ በዘላቂነት ለመፍታት ተግባብተናል::
መምህራኖች የትውልድ ግንባታ ስራችንን በመገንዘብ እዉቅና የሰጡ ሲሆን እኛም ላበረከቱት አስተዋፆኦ ሁሉ ከልብ አመስግነናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.