
በመዲናዋ በቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብር የተሰሩ ስራዎች በትውልድ ግንባታው ዘርፍ ልምድ የሚቀሰምበት መሆኑን የኬኒያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተናገሩ
ከኬኒያ ሞምባሳ የመጡ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሐ ግብር እየተከናወኑ የሚኙ ስራዎችን ጎብኝተዋል።
መዲናዋን ምቹ የህጻናት ማደጊያ ለማድረግ በቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሀ ግብር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የልኡክ ቡድኑ አባላት ገልጸዋል።
የቀጣይ ሀገር ተረካቢ ብቁ ትውልድን ለማፍራት በህጻናት ልማት ላይ የሚሰራው ስራ መሰረት መሆኑን የገለጹት የልኡኩ አባላት፣ አዲስ አበባም ይህንን የሚመጥን ስራ እያከናወነች ትገኛለች ብለዋል።
በመዲናዋ በቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር ከተሰሩ ስራዎች ብዙ ልምድ መቅሰማቸውን የገለጹት የልኡካን ቡድን አባላቱ፣ ህጻናትን መሰረት አድርገው የተሰሩ ስራዎች በትውልድ ግንባታው ዘርፍ ለመላው አፍሪካ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.