የአይዲ ፎር አፍሪካ 2025 ዓለም አቀፍ ዓመታዊ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአይዲ ፎር አፍሪካ 2025 ዓለም አቀፍ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በከተማችን እየተካሄደ ነው።

አዲስ አበባ እያስተናገደች ባለችው ዓለም ዓቀፉ የID4 for Africa 11ኛ ጉባኤ በፋይዳ ምዝገባ እና በወሳኝ ኩነት ቅንጅታዊ ትግበራ ላይ ልምዷን አቅርባለች።

ከተማችን የሲቪል ምዝገባ ሽፋንን በማስፋት ዘርፉን ለመለወጥ የተወሰደውን የከተማ አስተዳደሩ እርምጃ፣ ከፋይዳ ስርዓት ጋር እየተተገበረ ያለውን ቅንጅት እንዲሁም የተገኘውን ውጤት በመድረኩ አካፍላለች።

ኮንፈረንሱ የተጀመረውን ዲጂታል ብሄራዊ መታወቂያ /ፋይዳን / በተሟላ ሁኔታ እውን ለማድረግ የሚጠቅም ሲሆን አዲስ አበባም በዚህ ረገድ የተያዘዉን ራዕይ በፍጥነት እየተገበረች ነው።

የአይዲ ፎር አፍሪካን ጨምሮ የዓለም የስራ ድርጅት (ILO) እና ሌሎች ኮንፍራንሶች መከናወን የከተማችንን የኮንፍራንስ፣ የቱሪዝም እና የኤግዚቢሽን ማዕከልነት ከፍ በማድረግ እንዲሁም የስራ እድልን በመፍጠር ረገድ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ከመሆኑ ባሻገር የአዲስ አበባን ኢኮኖሚ ስለሚያነቃቃ የዚህ አይነት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.