.png)
"ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ የድርሻዉን በመወጣት ለቀጣዩ ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማስረከብ ይጠበቃል፡፡" የዉይይቱ ተሳታፊዎች
"የላቀ የጤና አገልግሎት ለሃገር ብልፅግና" በሚል መሪ ሃሳብ በመዲናችን በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰሩ የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች ዉይይት አካሄዱ
በመዲናዋ ባሉ በ11ዱም ክፍለ-ከተሞች በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰሩ የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች ዉይይት አካሂደዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት የለውጥ አመታት በሀገር አቀፍ እና በከተማ ደረጃ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በጤናው ዘርፍ የመጣው ውጤት አንዱና ዋናው መሆኑን ተናግረዋል ።
አክለዉም የዉይይቱ ዓላማ በሁለንተናዊ መልኩ እንደ ሀገርም ሆነ በጤናዉ ዘርፍ ለምናሳካቸዉ ዘርፈ ብዙ ስራዋች እና በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ ተወያይቶ የመፍትሄ አቃጣጫዎችን ለማምጣት ያለመ ነዉ ሲሉ ዶክተር ዮሐንስ ገልጸዋል ።
በዉይይቱም በከተማዋ በተሰሩና እየተሰሩ ባሉ የልማት ስራዎች እንዲሁም በጤናው ዘርፍ ያሉ ጠንካራ አፈፃፀሞችን ለማስቀጠል፤የተገኙ ዉጤቶችን ለማፅናት፤ክፍተቶችን ለማረም እና ተቀናጅቶ ይበልጥ ለመስራት እድል የፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ በተገኙ ስኬቶች የጤና ባለሙያዎች አበርክቶ የላቀ እንደነበረና ባጋጠሙ ችግሮች በሙያቸዉ የህይወት መስዋትነት ጭምር በመክፈል አርአያነታቸዉን ማስመስከር መቻላቸዉን ይህም ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት በዉይይቱ ተገልፃል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ ለሀገር እድገት እና ብልፅግና በሚደረገዉ እርብርብ ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ የድርሻዉን በመወጣት ለቀጣዩ ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጲያን ማስረከብ ይጠበቃል በማለት አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.