.png)
የንግዱ ማኀበረሰብ ለሀገር ዕድገት የማይተካ ሚና እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ
የንግዱ ማኀበረሰብ ለሀገር ዕድገት የማይተካ ሚና እያበረከተ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።
ምክትል ከንቲባው ነጋዴው በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ለከተማዋ ልማት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ''ለሁለንተናዊ ብልፅግና፤ የንግዱ ማኀበረሰብ ሚና'' በሚል መሪ ሐሳብ ፤ ከደረጃ 'ሀ' እና ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄዷል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች መንግስት በከተማዋ እያከናወነ በሚገኘው የልማት ሥራ ውስጥ አሻራቸውን በማሳረፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
የንግዱ ማኀበረሰብ ለሀገር የልማት ጉዞ በትኩረት መስራቱን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
መድረኩ የንግዱ ማህበረሰብ ባለፉት 7 የለውጥ ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶች የሚታዩበት፣ በአምራች ኢንዱስትሪው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚሰራበት እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
AMN
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.