
ዛሬ የኬንያ የሞምባሳ ግዛት አስተዳዳሪ አብዱልስዋማድ ሸሪፍ ናስርን እና የልዑካን ቡድናቸውን ወደ አዲስ አበባ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ተቀብለናቸዋል።
በቆይታችንም አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ ምቹ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ በቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር ያገኘናቸው ስኬቶችን እንዲሁም ሌሎች እንደ ልምድ ሊወሰዱ የሚገባቸው የከተማ ልማት ስራዎችን ለልዑካን ቡድኑ አቅርበናል።
የሞምባሳ ግዛት አስተዳዳሪ አብዱልስዋማድ ሸሪፍ ናስር ከተማችን አዲስ አበባ የስበት ማዕከል እና የተቀናጀ ከተማ ተምሳሌት ሆና የምትጠቀስ መሆኗን ገልጸውልናል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በአራት ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታቸው በከተማችን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም፣ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ፍሳሽ አስተዳደር፣ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታችንን እንዲሁም ኮሪደር ልማት ተኮር እና ሌሎች የከተማ ትራንስፎርሜሽን ስኬቶቻችንን በመጎብኘት ከከተማችን ጋር የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.