አዲስ አበባ የቱሪዝም ማዕከልነቷን እያረጋገጠች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ የቱሪዝም ማዕከልነቷን እያረጋገጠች ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ የቱሪዝም ማዕከልነቷን እያረጋገጠች መሆኗን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ከንቲባዋ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ጎብኝተዋል። 

በጉብኝታቸው ወቅት አዲስ አበባ በርካታ ትላልቅ ሁነቶችን እያዘጋጀች መሆኗን የገለጹት ከንቲባዋ፥ በዚህም የቱሪዝም ማዕከልነቷን እያረጋገጠች ነው ብለዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ትልቅ ውጤት እየመጣ መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህም ስማርት ሲቲን ለማጎልበት ትልቅ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ከግንቦት 8 ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው ኤክስፖ ላይ የሳይበር ደህንነትና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.