“አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ ግብር አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን አጽንኦት ሰጠተው አንሰተዋል። ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መሆኑን አውስተዋል። እንደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዮት፣ ዲጂታል መታወቂያ ብሎም “የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ” አይነት ፕሮግራሞቿ ኢትዮጵያ ሕልሞችን ወደ ተጨባጭ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተግባራት መለወጥ ችላለች። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በ2030 ማንም ወደ ኋላ በማይቀርበት አኳኋን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት አስምረውበታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.