.png)
"ለተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓትና ባህል ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ በከተማ ባሉ 11 ከተሞች የተውጣጡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉይይት አካሄዱ።
ዛሬ በአስራ አንዱም ክፍለከተሞች የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ባካሄዱት የጋራ ውይይት ላይ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በፓለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርቦ በመስራት እንደ ሀገር እየታዩ ያሉ ለዉጦችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የጋራ ምክርቤቱ ተወያዮች ገልጸው ከመንግስትጋ በመደማመጥና በመነጋገር የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የዳበረ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እንዲረጋገጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ወሳኝ መሆኑገልጸው አዲስ የፖለቲካ ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.