ለሚኩራ ክፍለከተማ ከቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ ሹኒ(...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለሚኩራ ክፍለከተማ ከቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ ሹኒ(Shunyi) ክፍለ ከተማ ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል::

ስምምነቱን የተፈራረሙት የለሚኩራ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ኮሚቴ ፀሀፊ Gong Zonagyuan ሲሆኑ በቀጣይ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በልማት፣ በኢንቨስትመንት እንዲሁም በንግድ ዘርፎች ዙሪያ ትብብር መፍጠር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል::

ሹኒ ክፍለ ከተማ (Shunyi) ትላልቅ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችና high-tech ኩባንያዎች የሚገኙባት ስትሆን ዘመናዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በዳበረ ትራንስፖርት መሰረተልማቷም ትታወቃለች፡፡

በአዲስ አበባና ቤጂንግ ከተሞች መካከል ያለውን የእህትማማች ግንኙነት መሰረት በማድረግ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከሹኒ ክፍለ ከተማ ጋር በትብብር ለመስራት የተፈራረሙ ሲሆን በቀጣይ በሀገራችን ትላልቅ የቢዝነስ አውደ ርዕይ በጋራ ለማዘጋጀት እና በኩነት ኢንዲስትሪ ልማት ለመተባበር ተስማምተዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.