"አዲስ አበባ እንደ ስሟ ፤ዉብ፤ሳቢ እና ፍንትዉ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"አዲስ አበባ እንደ ስሟ ፤ዉብ፤ሳቢ እና ፍንትዉ ብለዉ የሚታዩ አዳዲስ ገፅታዎችን በመላበሷ መልኳተቀይሯል፡፡" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከንቲባዋ ይህን ያሉት በካዛንቺስ የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ተገኝተዉ በሰጡት ማብራሪያቸዉ ነዉ፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በካዛንቺስ የኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራዎችን አስመልክተዉ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት ስናነሳ ስፋቱን ማየት መልካም ነዉ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአጠቃላይ ወደ 1ሺ ሄክታር መሬት የሸፈነ ይህም እስከ አዋሬ፤ቤይለር፤ ቀበና ድረስ የሚገጥም ነዉ ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት ብለን የምንጠራዉ ቸርቸር ጎዳናን ይዞ በለገሃር፤በሜክሲኮ እድርጎ በ4 ኪሎ የሚመጣዉን ጭምር የኮሪደር ልማት ዉስጥ ተካቶ እንዲለማና እኩል ደረጃ ላይ እንዲመጣ የተደረገ ነዉም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ኮርደር ልማቱን በምንሰራበት ሰዓት አንዱ ትልቁ መሰረተ ልማቶቻችንን ማገኛኘት ወይም ኔትዎርክድ ማድረግ በመሆኑ በቀበና ስንሄድ ከኮሪደር 1 ጋር ፤ወደ አዋሪ ስንሄድ ወደ 4ኪሎ ፤በእንደራሴ በኩልም ቀጥታ ሂዶ ካዛንቺስ ቶታል ጋር የሚገኛኙ መሆኑን ጠቅሰዉ በመለስ ፋዉንዴሽን ሲኬድም ቀጥታ  ወደ ቤተ መንግስቱ ከሚሄደዉ መንገድ እና ካዛንቺስ ቶታል ጋር ተመልሶ የሚገናኝና መስቀለኛ መንገዶቹም በተመሳሳይ ወደ ቦሌ  እና ወደ መገናኛ በሚያመጣዉ መገናኛ ናቸዉ ብለዋል፡፡

አያይዘዉም አዲስ አበባ ላይ መንገድ ለተሸከርካሪ ብቻ ነበር ያዉም ጠባብ መንገዶች ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሁን ግን መንገድ ለእግረኛ ፤ለሞተር አልባ  እና ለሌሎች ተሸከርካሪዎች አገልግሎት እንዲዉሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

56 የሚደርሱ ከቴክኖሎጂ ጋር የተቆራኙና ባህልን የሚያንፀባርቁ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ የተሰሩ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች መኖራቸዉን ጠቁመዉ በሁሉም ቦታዎች ላይ በማንኛዉም ደረጃ ላይ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተለያዩ አገልግሎቶች በጋራ የሚጠቀሙበት፤የሚዝናኑበት እና የሚያርፉበት እድልን የፈጠረ የልማት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አዲስ አበባን ስማርት ከተማ ከማድረግ ህልማችን ጋራ አያይዘን በጣም ከመሬት በታችም የመብራት የቴሌኮም፤የዉሃ፤የፍሳሽ እና የአይቲኤስ ወሳኝ የሆኑ መሰረተ-ልማቶች ተገንብተዋልም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም አዲስ አበባ እንደ ስሟ ፤ዉብና ሳቢ ፍንትዉ ብለዉ የሚታዩ አዳዲስ ገፅታዎችን በመላበሷ መልኳ ተቀይሯል ያሉት ከንቲባዋ በዚህም ጠቅላይ ሚኒስተራችን የሚያነሱት የትስስር ልማት ፅንሰ ሃሳብ  ወደ ተግባር ተለዉጦ ተጨባጭ ለዉጥ የታየበት የኮሪደር ልማት ስራችን ነዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.