ካዛንቺስ የብርቱ እጆች ውጤት የብልፅግና ሰው ተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ካዛንቺስ የብርቱ እጆች ውጤት የብልፅግና ሰው ተኮር ተግባር ተምሳሌት!

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በየደረጃው ያሉ የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ አመራሮች ፣ ሠራተኞችና የማህበረሰብ አንቂዎች የካዛንቺስ የኮሪደር ልማት ሥራን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክ/ከተማ  ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ዶ/ር አዲሱ ሻንቆ እንዳሉት የካሳንቺስ የኮሪደር ልማት ሥራ ዋና ዓላማው ከተማዋን ስታንዳርዷን ጠብቃ እንድትለማ ታሳቢ በማድረግ በርካታ ለህዝብ መዝናኛ አገልግሎት እና ለወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ እንዳሁም በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊ የሆኑት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በየደረጃው ያሉ የሚድያ ባለሙያዎችም ባዩት የኮሪደር ልማት ሥራ እጅግ በጣም የተደሰቱ  መሆናቸውንና በቀጣይ በመሰል የልማት ሥራዎች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የሚያደረጉ ፣ የተሰሩ ስራዎችንም ህብረተሰቡ አውቆዋቸው በቀጣይም የልማቱ ባለቤት እንዲሆን የሚሰሩ መሆኑን ገልጸዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.